loading
በደም የተጻፈ የኢትዮጵያ ታሪክ በብዕር ቀለም ሊለወጥ አይችልም-ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

አበባ፣ መስከረም 24፣ 2014 ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በደም የተጻፈ የኢትዮጵያ ታሪክ በብዕር ቀለም ሊለወጥ አይችልም ሲሉ ተናገሩ። ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ቀጣይ ሀገራዊ አቅጣጫን ያመላከቱበትን ንግግር አድርገዋል። ኢትዮጵያ በሀገረ መንግሥት ታሪኳ ጥቅሟን ለሌሎች አሳልፋ ሰጥታ እንደማታውቅ የገለጹት ፕሬዚዳንቷ፣ አሁንም ቢሆን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ከማንም ጋር አንደራደርም ብለዋል። እየተከተልነው ያለው ዲፕሎማሲ የኢትዮጵያን ክብር የማያስነካ እና ሉዓላዊነቷን የሚያስጠብቅ ሆኖ ይቀጥላል ሲሉም ተናግረዋል።

በምሥራቅ በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምሥራቅ ብዙ ፍላጎቶች የሚንፀባረቁ መሆኑን በመግለጽም፣ ኢትዮጵያ በቀጣናዋ የሚፈፀሙ ጉዳዮችን ከሩቅ ሆና አትመለከትም ብለዋል። ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላት ግንኙነት ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ ኢኮኖሚያዊ ትሥሥር እና የጋራ ብልጽግናን መሠረት ያደረገ እንደሚሆን ገልጸዋል።

ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትም በዙሪያችን ያሉ ጎረቤት ሀገራትን ያስቀደመ ሆኖ እንደሚቀጥል እና በትብብር እና በመግባባት ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የሚተገበር እንደሚሆንም አብራርተዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በታችኞቹ ሀገራት ላይ ጉልህ ጉዳት በማያስከትል መልኩ እንዲሁም
የኢትዮጵያን የመልማት መብት ጠብቆ የሚከናወን እንደሚሆንም ገልጸዋል።

በተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በየትኛውም ዓለም መብታቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ የሚሠራ መሆኑንም ጠቅሰዋል። እነዚህ ኢትዮጵያውያን የሀገራቸውን ገጽታ በመገንባት በሀገራቸው ጉዳይ በጉልህ እንዲሳተፉ በማድረግ በሀገራቸው ልማት ሚናቸውን እንዲወጡ ይሠራልም ብለዋል።
እኛ በኢትዮጵያ ያለን አማራጭ ተቻችሎ መኖር ነው፤ እኛ የአንድ ሀገር ልጆች ተቻችለን እና ተደማምጠን፣ ጥላቻን ተጠይፈን፣ ተወያይተን እና የሐሳብ ልዩነትን ተቀብለን ዘላቂነታችንን ማስጠበቅ የግድ ይጠበቅብናል ሲሉም አሳስበዋል። ከማንኛውም ፈተና በኋላ ብርሃን አለ፤ እጆቻችን በእሾህ ተወግተው እየደማ ከሆነ ጽጌረዳዋ ሩቅ አይደለችም የሚል ፍልስፍናን እንደ ምሣሴ በመጥቀስም፣ የእኛም ጽጌሬዳ ሩቅ አይደለችም እላለሁ ሲሉ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ:- http://artstv.tv/
ቴሌግራም:-https://t.me/Arts_tv

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *