loading
በዮርዳኖስ ድንገተኛ ጎርፍ የ18 ሰዎችን ህይወት ቀጠፈ

በዮርዳኖስ ድንገተኛ  ጎርፍ  የ18 ሰዎችን ህይወት ቀጠፈ

አርትስ 16/02/11

በዮርዳኖስ በደረሰ ድንገተኛ  የጎርፍ  አደጋ  18 ሰዎች ህይወታቸዉን አጡ፡፡

ሟቾቹ  አደገኛ በሆነዉ ሙት ባህር አቅራቢያ የነበሩ ተማሪዎችና መምህራን ናቸዉ ተብሏል፡፡አብዛኞቹም ከ 14 አመት በታች መሆናቸው ተነግሯል፡፡

ሚድል ኢስት ሞኒተር ሮይተርስን ጠቅሶ እንደዘገበዉ  34 ሰዎች አሁንም  በጎርፉ አደጋ ዉስጥ በመሆናቸዉ  የአደጋ ሰራተኞች ና የሀገሪቱ መከላከያ ሰራዊት ጭምር  በሂሊኮፕተር በመታገዝ ህይወት ለማዳን እየጣሩ ነዉ፡፡

በአደጋዉ ቁጥራቸዉ እስካሁን ያልታወቁ ሰዎችም አደጋዉ በደረሰበት አቅራብያ በሚገኝ ሾሁና የተባለ ሆስፒታል  እርዳታ እየተደረገላቸዉ ነዉ ተብሏል፡፡

አደጋዉ በድንገት ያለወቅቱ በዘነበ ከባድ ዝናብ ሳቢያ የደረሰ መሆኑም ተነግሯል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *