loading
በያዝነው ሳምንት ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ይጠበቃል::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2013  በያዝነው ሳምንት ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ይጠበቃል:: በኢትዮጵያ እና ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነመንግስታት ሀገራት ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ሊጥል እንደሚችል የምስራቅ አፍሪካ የአየር ንብረት የልህቀት ማዕከል አስጠንቅቋል፡፡ ማዕከሉ እንደገለጸው በተለይም በመካከለኛው እና ምዕራብ ኢትዮጵያ እና በሰሜን ምስራቅ ሶማሊያ አካባቢዎች ከባድ ዝናብ ሊጥል ይችላል፡፡

በእነዚህ ሀገራት የሚጠበቀው ከባድ ዝናብ ሊያደርስ የሚችለውን አደጋ ለመከላከልባለድርሻ አካላት ተገቢውን የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስዱ ነው ያስጠነቀቀው፡፡ትንበያው በሚቀጠሉት ሰባት ቀናት ውስጥ የሚጠበቅ ሲሆን በምዕራብ እና መካከለኛው ኢትዮጵያ ጥቂት ቦታዎች ከ 200 ሚሊ ሜትር በላይ ከባድ ዝናብ ይጠበቃል ነው የተባለው፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና በጎረቤት ሀገራት ደቡብ-ምዕራብ ሱዳን፣ከሰሜን-ምዕራብ እስከ ደቡባዊ-ምዕራብ ደቡብ ሱዳን፣በምዕራብ እና፣ሰሜን-ምስራቅ ሶማሊያ እንዲሁም በሰሜን-ምዕራብ ዩጋንዳ እና ምዕራብ ኬንያ ከ 50 እስከ 200 ሚሊ ሜትር የሆነ መካከለኛ ዝናብ ይጠበቃል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *