በኮተቤ አርማታ በመሞላት ላይ ያለ የድልድይ ግንባታ ተደርምሶ 15 ሶዎች ላይ ጉዳት ደረሰ
በኮተቤ አርማታ በመሞላት ላይ ያለ የድልድይ ግንባታ ተደርምሶ 15 ሶዎች ላይ ጉዳት ደረሰ
የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ ልዩ ስሙ ማርያም ቤተክርሲቲያን አጠገብ አርማታ በመሞላት ላይ ያለ የድልድይ ግንባታ ተደርምሶ 15 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል
የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ሃለፊ አቶ ንጋቱ ማሞ ለአርትስ ቲቪ እንደገለፁት ትላንት እረፋድ 4 ሰዓት ላይ አደጋው የደረሰ ሲሆን በዚህም በ 15 ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል ጉዳት መድረሱን ተናግረው የሞተ ሰው ግን የለም ብለዋል፡፡
ሃላፊው በመደርመስ አደጋው የተጎዱ እና የተሸፈኑ ሰዎችን ለማዳን የባለስልጣኑ ሰራተኞች እስከ ሊሊቱ 6 ሰዓት ድረስ ቁፋሮ እያከናወኑ መቆየታቸውን ገልፀው አሁንም ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ነግረውናል፡፡
በተያያዘም መንገዱን በዋናነት የሚያስገነባው የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን የኮምዮኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሮክተሬት ዳይሬክተር አቶ ጡማይ ወ/ገብርኤል ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት አደጋው በምን ምክንያት እንደተከሰተ በማጣራት ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
አቶ ጡማይ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የኮተቤ መምህራን ኮሌጅ የዋና መንገድ ግንባታ ከተጀመረ አንድ አመት የሞለው መሆኑን አስታውሰው ፤ግንባታውን በቀጣዩ አመት ለማጠናቀቅ ታስቧል ብለውናል ፡፡
የመንገዱን ግንባታ ተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን የሚሰራው ሲሆን የማማከሩን ስራ ደግሞ ዩኒ ኮን የተባለው ድርጅት እንደሚያከናውነው ሰምተናል፡፡