loading
በክልሎች መካከል እና በትምህርት ተቋማት ላይ እየተፈጠረ ላለ ብሔር ተኮር ግጭት አቀናባሪዎች እና ወንጀል ፈፃሚዎችን ህግ ፊት ለማቅረብ የተደራጀ ምርምራ እየተካሄደ ነው ተባለ፡፡

በክልሎች መካከል እና በትምህርት ተቋማት ላይ እየተፈጠረ ላለ ብሔር ተኮር ግጭት አቀናባሪዎች እና ወንጀል ፈፃሚዎችን ህግ ፊት ለማቅረብ የተደራጀ ምርምራ እየተካሄደ ነው ተባለ፡፡

ይሄንን ያለው የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የ5 ወር የሥራ ክንውኑን ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያቀርብ ነው፡፡

በተፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት የዜጎች የመንቀሳቀስ መብት መገደቡን፣ ዜጎች መሞታቸውንና ከመኖሪያቸው መፈናቀላቸው እንዲሁም ንብረታቸው መዘረፉንና መውደሙን ያስታወሰው የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ለዚህ ምክንያት ናቸው ያላቸውን ሕግ ፊት ለማቅረብ ከክልሎች ጋር በመተባበር ምርመራ አድርጊያለሁ ብሏል፡፡

በምርመራው ውጤት መሰረትም ክስ የመመስረት ሂደት መጀመሩን ዋና ዐቃቤ ህግ ብርሃኑ ፀጋዬ ለምክር ቤቱ አስረድተዋል፡፡

ሕግ ፊት የሚቀርቡት በወንጀል የተሳተፉት ብቻ ሳይሆኑ ነገሩን ከጀርባ ሆነው ያስተባበሩ፣ የገንዘብ ድጋፍ ያደረጉ ጭምር እንዲሆኑ በሚያስችል ሁኔታ መረጃ እየተሰበሰበ መሆኑን ተነግሯል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *