loading
በኬንያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ለመሳተፍ ቃል ቀቡ

በኬንያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ለመሳተፍ ቃል ቀቡ

በኬንያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በማሰባሰብ ተሳታፊ ለመሆን ቃል ገብተዋል

በኬንያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተለያዩ ስብስቦች ናይሮቢ ከሚገኘው የኢፌዲሪ ኤምባሲ ጋር ባዘጋጁት ዝግጅት በመጪው ሚያዚያ 12 ቀን 2011 ዓ.ም. የሚካሄደውን የትረስት ፈንድ ዝግጅት ለመደገፍ አስተዋጽኦ ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል።

ኢትዮጵያውያኑ ፕሮግራሙን የሚያስተባብር ኮሚቴ በማቋቋም ዝግጅት እያደረጉ ሲሆን በሀገራቸው እየተካሄደ ለሚገኘው ለውጥ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

በኬንያ የኢፌዲሪ አምባሳደር መለስ ዓለም በውጪ የሚኖሩ ዜጎች የሀገራቸው እንደራሴ በመሆናቸው በገጽታ ግንባታ፣ ልማት እና ሌሎችም መስኮች አስተዋጽኦ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል ።

አምባሳደር መለስ በውጭ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በየቀኑ ቢያንስ አንድ ዶላር በመለገስ ለተለያዩ የልማት ሥራዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *