በከተማችን ከሚገኙ 130 ሪል እስቴት አልሚዎች ዉስጥ ስድስቱ ብቻናቸዉ የሚጠበቅባቸዉን ግብር የከፈሉት ተባለ፡፡
በከተማችን ከሚገኙ 130 ሪል እስቴት አልሚዎች ዉስጥ ስድስቱ ብቻናቸዉ የሚጠበቅባቸዉን ግብር የከፈሉት ተባለ፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር የሬል እስቴት አልሚዎች እና ባለቤቶች ያሉባቸውን ችግሮች በተመለከተ የአስጠናውን ሪፖርት ሲያቀርብ ነዉ ይህንን የገለጸዉ፡፡
ጥናቱ ለባለሀብቶች እና ለመንግስት ባለድርሻ አካላት ይፋ ሲደረግ በከተማችን የሚገኙ 130 የሪል እስቴት ህንፃ አልሚዎች አብዛኞቹ ግብር ለመክፈል ቸልተኛ መሆናቸው ተነግሯል፡
የገቢዎች ሚኒሰቴር የገቢዎች ጥናት አጣሪ ኮሚቲ ወ/ሮ ሰብለ ገ/እግዚአብሄር እንዳሉት በከተማችን ከሚገኙ 130 የሪል ስቴት ህንፃ አልሚዎች መሀከል 6ቱ ብቻ የግብር ግዴታቸውን በአግባቡ የተወጡ ሲሆኑ ቁጥራቸው 21 የሚሆኑት ደግሞ በተቆራረጠ መልኩ የሚከፍሉ መሆናቸው ተነግሯል፡፡ ቀሪዎቹ 103 ሪል ስቴቶቹ ግን የግብር ግዴታቸውን እንዳልተወጡ ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም 130 የሚሆኑት የሬል ስቴት አልሚዎች ከያዟቸው 4 ሚሊዮን ካሜ በላይ መሬት መንግስት ማግኝት የሚገባውን ገቢ አጥቷል፡፡
ዘገባዉ የአቢ ፍቃዱ ነዉ፡፡