loading
በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የ21ኛ ሳምንት መርሃግብር ዛሬ ሶስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ

በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የ21ኛ ሳምንት መርሃግብር ዛሬ ሶስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ

የሊጉ የበዓል ሰሞን ጨዋታዎች ቀጥለው እየተከናወኑ ሲሆን በዛሬው የአውሮፓውያኑ አዲስ ዓመት ዕለት በ21ኛ ሳምንት መርሃግብር ሶስት ያህል ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡

ቀን 9፡30 ጉዲሰን ፓርክ ላይ በማርኮ ሲልቫ የሚሰለጥነው ኢቨርተን ሌስተር ሲቲን ይገጥማል፡፡

አመሻሽ 12፡00 የኡናይ ኢምሪው አርሰናል በኢምሬትስ በክላውዲዮ ራኔሪ የሚመራውን ፉልሃም ያስተናዳል፤ አሰልጣኝ ኡናይ ኢምሪ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሽንፈት እና ነጥብ መጣል የተጠናወታቸው ሲሆን መገናኛ ብዙሀኑ ከቪንገር የመጨረሻ ዘመን ጋር እያስተያዩት ነው፤ በጉዳት ምክንያት በሊቨርፑሉ ጨዋታ አልተሰለፈም የተባለውን ሜሱት ኦዚልንም የመሰለፍ ዕድል ሊሰጡት እንደሚችሉ ተጠቁሟል፤ ተከላካዩ ናቾ ሞንሪያል ከጉዳት እየታገለ ሲሆን ሮብ ሆልዲንግ ፣ ሄንሪክ ሚኪታሪያን እና ዳኒ ዌልቤክ የረዥም ጊዜ ጉዳት ያለባቸው ተጫዋቾች ናቸው፡፡

አርሰናል በማንኛውም ውድድር በ114 ዓመት ጊዜ ውስጥ በሜዳው በፉልሃም ሽንፈት ገጥሞት አያውቅም፡፡

በካርዲፍ ሲቲ ስታዲዮም ካርዲፍ ቶተንሃምን ምሽት 2፡30 ላይ ይገጥማል፡፡ አሰልጣኝ ኒል ዋርኖክ አዲስ ጉዳት ያለበት ተጫዋች የላቸውም ተብሏል፡፡ የስፐርሱ ቀኝ ተከላካይ ሰርጌ ኡርዬ ከጉዳት ተመልሶ ቡድኑን እንደሚቀላቀል ይጠበቃል፤ ነገር ግን ቪክተር ዋንያማ፣ ያን ቬርቶህን፣ ሙሳ ዴምቤሌ፣ ኢሪክ ዳየር እና ኢሪክ ላሜላ ይህ ጨዋታ ያመልጣቸዋል ብሏል ፡፡

ሁለቱ ቡድኖች በተገናኙባቸው የመጨረሻ አራት የፕሪምየር ሊግ  ጨዋታዎች ላይ ቶተንሃም ድል አድርጓል፡፡

የሊጉ የ21ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ነገ ሲጥሉ ምሽት 4፡45 በርንማውዝ ከ ዋትፎርድ፣ ቼልሲ ከ ሳውዛምፕተን፣ ሀደርስፊልድ ከ በርን፣ ዌስት ሃም ከ ብራይተን ፣ ወልቭስ ከ ክሪስታል ፓላስ እንዲሁም ምሽት 5፡00 ኒውካስትል ከ ማንችስተር ናይትድ ይፋለማሉ፡፡

ሀሙስ የመጨረሻው ተጠባቂ ጨዋታ በማንችስተር ሲቲ እና ሊቨርፑል መካከል ይከናወናል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *