loading
በኢንዶኔዥያ በደረሰው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ 189 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ

በኢንዶኔዥያ በደረሰው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ 189 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ

አርትስ 19/02/2011

 

 ትናንት ሌሊት 189 ሰዎች አሳፍሮ ከኢንዶኔዢያ ዋና ከተማ ጃካርታ የተነሳው አውሮፕላን ከደቂቃዎች በኋላ ድንገት ጃካርታ ባህር ውስጥ መከስከሱ ታወቀ።

በአደጋው ተሳፋሪዎቹ በሙሉ አልቀዋል እየተባለ ነው።

ንብረትነቱ የኢንዶኔዥያ የሆነው ይኸው ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ከተነሳ 13 ደቂቃ በኋላ ድንገት ከዋናው ጣቢያ ጋር የነበረው ግንኙነት ተቋርጦ ነበር ተብሏል።

ዘኢስት አፍሪካን ዛሬ እንደዘገበው አውሮፕላኑ የሚያመራው ፓንግካል ፒናንግ ወደተባለችው የኢንዶኔዢያ ሌላዋ ከተማ ነበር።

የአውሮፕላኑን መከስከስ ማረጋገጣቸውን የተናገሩት የሃገሪቱ ባለስልጣናት ከባህር ውስጥ አስከሬን ለማውጣት ፍለጋ መጀመሩንም ተናግረዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *