loading
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች ይከናወናሉ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች ይከናወናሉ
ሊጉ የ13ኛ ሳምንት መርሃግር በአዲስ አበባ እና በክልል ስታዲየሞች ላይ በሚከናወኑ አራት ያህል ጨዋታዎች ዛሬ ይጀመራል።
ክልል ላይ በተመሳሳይ 9፡ 00 ሶስት ጨዋታዎች ሲደረጉ በስቱዋርት ሆል የሚመራው ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ትግራይ አቅንቶ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር ይጫወታል፡፡ ጎንደር ላይ ደግሞ 5ኛና እና 6ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት ፋሲል ከነማ እና አዳማ ከተማ በፋሲለደስ ስታዲም ይገናኛሉ፡፡ ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘው ደቡብ ፖሊስ የትግራዩን መቐለ 70 እንደርታ ሀዋሳ ላይ የሚገጥም ይሆናል፡፡
በዕለቱ ዘግይቶ የሚጀምው የኢትዮጵያ ቡና እና ጅማ አባ ጅፋር ጨዋታ ሲሆን በአዲስ አበባ ስታዲየም 10፡00 ሲል ይካሄዳል፡፡ ቡናማዎቹ ከተከታታይ ድል በኋላ መቐለ ላይ በ12ኛ ሳምንት መርሀግብር ሽንፈት አስተናግደው የተመለሱ ሲሆን የጅማው ቡድን በአንፃሩ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ከተሰናበተ በኋላ ሜዳው ላይ ሶስት ነጥብ አሳክቷል፡፡
ዛሬ ድሬዳዋ ላይ በድሬዳዋ ከነማ ከ ሲዳማ ቡና መካከል ሊደረግ የነበረው ግጥሚያ በአካባቢው ባለው ወቅታዊ አለመረጋጋት ለሌላ ጊዜ ተራዝሟል፡፡
ሊጉ በዕለተ በሶስት ግጥሚያዎች ሲቀጥል፤ ባህር ዳር ከነማ ወደ ወላይታ አምርቶ ሶዶ ላይ ወላይታ ድቻን 9፡00 ሲል የሚገጥም ይሆናል፡፡ በተመሳሳይ ሰዓት በትግራይ ደርቢ መቐለ ላይ ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኙት ደደቢት እና ስሑል ሽረ ይጫወታሉ፤ በአዲስ አበባ ስታዲየም መከላከያ ከሀዋሳ በ11፡00 ይፋለማሉ፡፡
ሊጉን ኢትዮጵያ ቡና በ22 ነጥቦች ይመራል፤ ፈረሰኞቹ አንድ ተስተካካይ ግጥሚያ እየቀራቸው ከቡና በአንድ ነጥብ አንሰው በ21 ነጥቦች ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ሀዋሳና እና ሲዳማ ቡና በተመሳሳይ 20 ነጥቦች በግብ ክፍያ ተበላልጠው ሶስተኛና አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን ዳዋ ሆቴሳ ከአዳማ እና አዲስ ግደይ ከሲዳማ በ8 ጎሎች ሲመሩ የሀዋሳው ታፈሰ ሰለሞን በ7 ጎል ይከተላል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *