loading
በኢትዮጵያ የበጎ ፈቃደኝነትን ባህል ማሳደግ እንደሚገባ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ገለጹ

በኢትዮጵያ የበጎ ፈቃደኝነትን ባህል ማሳደግ እንደሚገባ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ገለጹ

አርትስ 02/04/2011

ፕሬዝደንቷ ትናንት የተከበረውን የአለም የበጎ ፈቃደኞች ቀን በማስመልከት የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ባዘጋጀው መድረክ ላይ እንዳሉት በኢትዮጵያ በአነስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውን የበጎ ፈቃደኝነት ባህል ለማጎልበት መስራት ይገባል፡፡
በሃገራችን የበጎ ፈቃደኝነት ባህል እንዲዳብር መንግስት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን የጠቀሱት ፕሬዝደንቷ ለዚህም ማሳያ በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አነሳሽነት ወጣቶች በበጎፈቃደኝነት ተደራጅተው ወደ ተለያዩ ክልሎች እንዲሄዱ መደረጉን አስታውሰዋል፡፡
ፕሬዝደንት ሣሕለወርቅ ዘውዴ እንዳሉት በአሁኑ ወቅት ሃገራችን ከእያንዳንዱ ዜጋ የምትፈልገው ብዙ ነገር አለ፡፡ በመሆኑም የበጎ ፈቃደኝነት ባህልን በማሳደግና እሴቱን በማስፋፋት ለሃገራዊ ልማትና ብልጽግና መረባበረብ እንደሚገባ ነው የተናገሩት፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *