loading
በኢትዮጵያ የቆዳ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችን ያሳተፈው ዓለም አቀፍ የንግድ ኤግዚቢሽን በፈረንሳይ ፓሪስ እየተካሄደ ነዉ።

አርትስ 02/01/2011
በኤግዚቢሽኑ በአገራችን የቆዳ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ጥቁር አባይ ጫማ፣ ራምዚ፣ ሂርኮ እና ሌሎችም ኩባኒያዎች የተለያዩ የቦርሳ፣ ጫማ እንዲሁም አልባሳትን በማቅረብ በጃፓኑ ዓለምአቀፍ የትብብር ኤጀንሲ (JICA) ስፖንሰር አድራጊነት ለመጀመሪያ ጊዜ በፈረንሳይ የአገራችንን የቆዳ ውጤቶች ማስተዋወቅ እንደተቻለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት በፌስቡክ ገፁ አስነብቧል።
በፈረንሳይ የኢፌዲሪ አምባሳደር አሊ ሱሌይማን በኤግዚብሽኑ የተገኙ ሲሆን ‹‹Ethiopian Highland Leather›› የተሰኘው ብራንድ በአውሮፓ ህብረት እንዲመዘገብ ክትትል እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *