loading
በኢትዮጵያ እየታየ ያለው ለውጥ ለሌሎች ሀገራት ምሳሌ መሆኑ ተገለፀ

አርትስ 22/01/2011 ዓ.ም

በሱዳን የኢ.ፈ.ዲ.ሪ ልዩ መልእክተኛ ባለሙሉ ስልጣን  አምባሳደር ሽፈራው ጃርሶ በሱዳን የአውሮፓ ህብረት አምምሳሌባሳደር ጂን ማይክል ዱሞንድ ጋር ተወያይተዋል።

ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር በተለያዩ መስኮች በጋራ እንደምትሰራ ጠቅሰው፤ በአገሪቱ እየታየ ያለው ለውጥና እድገት ለሌሎች ጎረቤት አገራት  መሆኑን አምባሳደር ጂን ገልጸዋል።

አምባሳደር ሽፈራው በተመሳሳይ መልኩ አዲስ ከተሾሙት የሱዳን ውሀ፣ መስኖና መብራት ሚኒስትር ኢንጂነር ከድር ሞሀመድ ጋር ተወያይተዋል።

ኢትዮጵያ እና ሱዳን የሚጋሩትን የውሀ ሀብት አስመልክቶ በጋራ ይበልጥ ለመስራት በሚችሉበት ሁኔታ እንዲሁም በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረዋል።

አምባሳደሩ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ብዙ ዓመታትን ያስቆጠረ መሆኑና ተጠናከሮ እንዲቀጥል መስራት ተገቢ እንደሆነ አስታውቀዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *