loading
በኢትዮጵያ ትንባሆን ህዝብ በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ላይ ማጨስ የሚከለክል ህግ ተግባራዊ አልተደረገም ተባለ

አርትስ 28/02/2011

ይህ የተባለዉ በጤና ልማት እና ፀረ-ወባ ማህበር አስተባባሪነት በአዲስ አበባ በተመረጡ ቦታዎች በዘመናዊ መሳሪያ በመታገዝ የተደረገ ጥናት በቀረበበት ወቅት ነው፡፡

ጥናቱ በተለይ ትንባሆን የማያጨሱ ሰዎች ያላቸውን ተጋላጭነት መጠን ለማወቅ የተደረገ መሆኑን ጥናት አቅራቢው አቶ ደረጀ ሽመልስ ተናግረዋል ፡፡

በከተማዋ አስሩም ክፍለ ከተሞች 47 በሚሆኑ ሬስቶራንቶች እና የምሽት መዝናኛ ቦታዎች የትንባሆ ጪስ ብክለት መጠንን በሚለካ መሳሪያ በታገዘው ጥናት መሰረት ሺሻ በሚጨስባቸው ቦታዎች  ከማይጨስባቸው   በ11 እጥፍ  ከፍ ብሏል፡፡

ትንባሆ በሚጨስባቸው ቦታወች ከማይጨስባቸው ጋር ሲነጻጸር ደግሞ 2 እጥፍ  ከፍ ያለ መሆኑን ጥናቱ ያስረዳል፡፡

መዝናኛ ቦታዎች ለአጫሾች ብቻ የማጨሻ ቦታ እንዲያዘጋጁ የሚያስገድድ ህግ ቢኖርም አፈጻጸሙ ላይ ክፍተት መኖሩም በመድረኩ ተነስቷል፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *