loading
በኢትዮጵያ በአማካኝ በአመት 60 ሺ ሰዎቸ በካንሰር ይያዛሉ ተባለ

አርትስ 23/02/2011

 

ከነዚህም ውስጥ 40 ሺ የሚሆኑት ሴቶች  ሲሆኑ 44 ሺዎቹ ደግሞ በተለያየ ግዜ   እንደሚሞቱ ተነግሯል ፡፡

የኢፌድሪ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ክፍል ባቀረበው ጥናት

በተለይም በኢትዮጵያ ውስጥ  የጡት ካንስር  ግንባር ቀደም ከሆኑ የካንሰር አይነቶች ቀዳሚው መሆኑ ተገልጽዋል ፡፡

በሚኒስቴሩ የማይተላለፉ በሽታዎች ዲፓርትመንት ባለሞያ ዶክተር ኩኑዝ አብደላ እንደተናገሩት   በኢትዮጵያ ውስጥ ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎችች ትኩረት እንደማይሰጥ በጥናቱ  አንስተዋል፡፡

ትኩረት ማጣቱም በካንሰር የመያዙ ቁጥር  ከጊዜ ወደ ጊዜ  ከፍ  እንዲል አድርጎታል ለዚህ ዋንኛው ምክንያት ደግሞ ፤ የካንሰር ህክምና የሚሰጡ ተቋማት ማነስ  የቅድመ ግንዛቤ ዕጥረት እና  የመድሃኒት አቅርቦት  እጥረት በዋናነት  የሚጠቀሱ ናቸው ብለዋል ፡፡

በአለም በየአመቱ ከ18 ሚሊዮን በላይ ሰዎች አዲስ የካንሰር ታማሚዎች የሚመዘገቡ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 9 ሚሊዮን ያህሉ ይሞታሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *