loading
በኢራቅ በኮሮና ቫይረስ ማገገሚያ ማዕከል በተነሳ የእሳት አደጋ የበርካታ ሰዎች ህይዎት ማለፉ ተሰማ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 6፣ 2013 በኢራቅ በኮሮና ቫይረስ ማገገሚያ ማዕከል በተነሳ የእሳት አደጋ የበርካታ ሰዎች ህይዎት ማለፉ ተሰማ፡፡

በማገገሚያ ማዕከሉ በተቀሰቀሰው ቃጠሎ ከ64 በላይ ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ 70 የሚሆኑት ደግሞ ቀላልና ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው የሀገሪቱ ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡

ፖሊስ የእሳት አደጋው መንስኤ በውል ባይታወቅም በሆስፒታሉ የሚገኝ ኦክስጂን መፈንዳት የአደጋው ሳይሆን እንዳልቀረ ነው የገለጸው፡፡

አደጋውም የደረሰው በናሲሪያ ከተማ አል ሁሴን ሆስፒታል ውስጥ መሆኑን የከተማዋ ፖሊስ አስታውቋል::
ማገገሚያ ማዕከሉ ከሶስት ወራት በፊት የተገነባ ሲሆን እስከ 70 ታካሚዎችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ ይቸላል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ሀገሪቱ ላይ ተንሰራፍቶ የቆየው አለመረጋጋት ሆስፒታሎች የኮቪድ-19 ወረርሽኝን መቋቋም እንዳይችሉ አድርጓቸዋል ሲሉ የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡
በኮቪድ ማገገሚያ ማእከሉ የተቀሰቀሰውን የእሳት አደጋ ተከትሎ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባዎች ተቃውሞ መቀስቀሱም ተሰምቷል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *