loading
በአገር አቀፍ ደረጃ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚደረግ ውይይትና ድርድር የሚመራበት ህግ ሊዘጋጅ ነው

አርትስ 19/03/2011

በአገሪቱ የሚገኙ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል በአገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚደረጉ ውይይቶችአካሄድ ላይ በጠቅላይ ሚኒስትሩ መነሻ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በዚህም ውይይቱና ድርድሩ የሚመራበት ህግ እንደሚዘጋጅ ተነግሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አበይ አህመድ እንዳሉት በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚካሄዱ ውይይቶች ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሚያወጣው መርሃ ግብር መሰረት ይካሄዳሉ።

በአገር አቀፍ ደረጃ በአዲስ መንፈስ መወያየትና በሃሳብ ብቻ መሸናነፍ ላይ የተመሰረተ አዲስ የፖሊቲካ ባህል መፍጠር የዚህ ውይይት ዋና ዓላማ እንደሆነም ተናግረዋል።

የውይይቱ አካሄድ በቅደም ተከተል የተቀመጠ ሲሆን ቀዳሚው ለሰከነ ፖሊቲካ ውይይት አመቺ የሆነ የመረጋጋትና የደህንነት ጉዳይ መፍጠር ነው ተብሏል።

የዴሞክራሲ ስርዓትና ባህል መገንባትና ዘላቂ የተረጋጋ ፖለቲካ ስርዓት ግንባታ መፍጠር እንደየቅደም ተከተላቸው ተግባራዊ የሚደረጉ ይሆናሉ እንደጠቅላይ ሚኒሰትሩ ገለጻ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ጉባዔ አዳራሽ በተካሄደው ውይይት ከውጭ አገራት የተመለሱትን ጨምሮ 80 የሚሆኑ አገር አቀፍና ክልላዊ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ተሳታፊ ነበሩ።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *