በአዲስ አበባ የተጀመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶች በአፋጣኝ ተጠናቅቀው ወደ አገልግሎት እንዲገቡ ይደረጋል ተባለ።
በአዲስ አበባ የተጀመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶች በአፋጣኝ ተጠናቅቀው ወደ አገልግሎት እንዲገቡ ይደረጋል ተባለ
የከተማው ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በመንገድ ግንባታ ዘርፍ ለሚሳተፉ የአልሚ እና አማካሪ ድርጅቶች የከተማ አስተዳደሩ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ላይ ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡
ምክትል ከንቲባው አስተዳደሩ በመንገድ ግንባታው ዘርፍ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ከገንቢ እና አማካሪ ድርጅቶች ጋር ተቀራርቦ ከመስራት በተጨማሪ ግንባታዎችን በሚያጓትቱ ድርጅቶች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቀዋል፡፡
በዘላቂነትም የመሠረተ ልማት ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ በከንቲባው የሚመራ የውሃ፣ የቤቶች እና የመንገድ ዘርፉን ያካተተ ቦርድ የማዋቀር ስራም እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የመንገድ ግንባታ ላይ የሚሳተፉ ገንቢ እና አማካሪ ድርጅቶች፤ የከተማ አስተዳደሩ ከዚህ በኃላ የሚገነቡ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ብቃትን ብቻ መሠረት ባደረገ መልኩ እንደሚሰጥ ማወቅ ይገባቸዋል ያሉት ምክትል ከንቲባው አሁን በግንባታ ላይ ያሉ እና እየተጓተቱ ያሉ ፕሮጀክቶችን በውል ጊዜያቸው አጠናቅቀው ለአገልግሎት ክፍት እንዲያደርጉም አሳስበዋል ። መረጃው የከንቲባ ፅ/ቤት ነው፡፡