loading
በአዲስ አበባ የሚገኙ 26 የግል የትምህርት ተቋማት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ባስከተለባቸው የኢኮኖሚ ጫና የሙያ ፈቃዳቸውን መለሱ።

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2013 በአዲስ አበባ የሚገኙ 26 የግል የትምህርት ተቋማት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ባስከተለባቸው የኢኮኖሚ ጫና የሙያ ፈቃዳቸውን መለሱ።የከተማ አስተዳደሩ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ባለስልጣን እንዳስታወቀዉ  ከእነዚህ መካከል 11 መዋዕለ ህጻናት፤ 13 የአንደኛ ደረጃና ሁለቱ ደግሞ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ናቸዉ፡፡

670 የግል የትምህርት ተቋማት ደግሞ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማግኘታቸውም ተገለጿል።የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሸዊት ሻንካ የነባር የግል ትምህርት ተቋማት የሙያ ፈቃድ በየሁለት ዓመት እንደሚታደስ ገልጸዋል። በዚሁ መሰረት ለትምህርት ዘመኑ 699 የግል ትምህርት ቤቶች የሙያ ፈቃድ ማረጋገጫ እንዲታደስላቸው ባለስልጣኑን ጠይቀዋል።

መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረትም የትምህርት ተቋማቱ ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶች ተፈትሸው ለ321 መዋዕለ ህጻናት፤ ለ207 አንደኛ ደረጃና ለ46 ሁለተኛ ደረጃ በድምሩ ለ574 ነባር ትምህርት ቤቶች እውቅና ተሰጥቷል ነው ያሉት። ኮቪድ-19 ባሳደረው ኢኮኖሚያዊ ጫና ምክንያት ማሟላት ያሉባቸውን መስፈርቶች በመጠኑ ያላሟሉ ነገር ግን የትምህርት ሂደቱን ለማስቀጠል ችግር የሌለባቸው መለየታቸውንም ገልጸዋል።

 በዚህም ለ59 የግል ትቤቶች የአንድ ዓመት ማስጠንቀቂያ በመስጠት ያሉባቸውን ክፍተቶች በአጭር ጊዜ በማረም በ2013 ዓ.ም ወደ ማስተማር ሂደት እንዲገቡ ይሆናል ብለዋል። ባለስልጣኑ ትምህርት ቤቶቹ የትምህርት ጥራትን ብሎም ወረርሽኙን ለመከላከል እያደረጉ ስላለው ቅድመ ዝግጅት የሚከታተሉና የሚቆጣጠሩ ባለሙያዎችን በሁሉም ክፍለ ከተሞች ማሰማራቱም ተገልጿል።በአዲስ አበባ 532 የመንግስትና 1 ሺህ 590 የግል በድምሩ 2 ሺህ 122 የትምህርት ተቋማት ይገኛሉ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *