loading
በአየር ብክለት ምክንያት ከ400 ሺህ በላይ ህፃናት ህይዎታቸው ማለፉን አንድ ጥናት አመለከተ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013በፈረንጆቹ 2019 በአየር ብክለት ምክንያት ከ400 ሺህ በላይ ህፃናት ህይዎታቸው ማለፉን አንድ ጥናት አመለከተ::ሄልዝ ኢፌክት ኢንስቱትዩት የተባለ ተቋም እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2019 በዓለማችን 476 ሺህ ጨቅላ ህፃናት የአየር ንብረት ለውጥ ባስከተለው ችግር ሳቢያ ህይዎታቸው ማለፉን በጥናት አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡ከነዚህ የችግሩ ሰለባ ከሆኑት ህፃናት መካከል አብዛኞቹ ከህንድና ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት ናቸው ተብሏል፡፡

አልጀዚራ በዘገባው እንዳስነበበው ከሟቾቹ ህፃናት መካከል 116 ሺህ ያህሉ ከህንድ 260 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ከአፍሪካ ናቸው፡፡ችግሩን አጠናሁ ያለው ተቋም እንደሚለው ከሆነ ህፃናቱ ለሞት የተዳረጉት በአብዛኛው በአካባያዊና በቤት ውስጥ ጭምር በሚፈጠር ብክለት ነው፡፡በአየር ብክለቱ ህዎታቸው ከለፈው ህፃናት መካከል አብዛኞቹ ዕድሜያቸው ከአንድ ወር ያላለፈ መሆኑም በጥናት ሪፖርቱ ተመልክቷል፡፡ሁኔታው በተለይ ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ እና ለደቡባዊ እስያ ሀገራት በእጅጉ አሳሳቢ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ነው አጥኝዎቹ ጥሪ ያቀረቡት፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *