loading
በአቶ ገላሳ ዲልቦ የሚመራው የሽግግር ኦነግ አመራሮች ከኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ጋር ተወያዩ

በአቶ ገላሳ ዲልቦ የሚመራው የሽግግር ኦነግ አመራሮችኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ጋር ተወያዩ

በአቶ ገላሳ ዲልቦ የሚመራው የኦነግ የአመራር ቡድን መንግስት ያደረገለትን ጥሪ ተከትሎ ባሳለፍነው ሳምንት ወደ ሀገር ቤት ከተመለሰ በኋላ ከኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ተገናኝቶ ተወያይቷል።

በርዕሰመስተዳድሩ ጽህፈት ቤት በተካሄደው የሁለቱ አካላት ውይይት የኦነግ አመራሮች የተደረገላቸውን ጥሪ ተቀብለው በሰላማዊ ትግል ለመካፈል ወደሃገር ቤት በመግባታቸው አድናቆት ተችሯቸዋል።

ርዕሰመስተዳድሩ አቶ ለማ መገርሳ በውይይቱ ወቅት የኦነግ ነባር አመራሮች ሲያደርጉት ለነበረው ትግል ምስጋና አቅርበዋል።

ሁላችንንም ከቤት ያስወጣን ለኦሮሞ ህዝብ ትግል ነው ያሉት አቶ ለማ መገርሳ ተለያይተን ብንቆይም ዛሬ አንድ ላይ ተቀምጠን መነጋገራችንና በጋራ ለመስራት መስማማታችን ለኦሮሞ ህዝብ ትግል ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ ነው ብለዋል።

የኦሮሞ ህዝብ አሁን ያገኘውን ድል ወደ ቀጣይ ምእራፍ ለማሸጋገር መደጋገፍ እና አብሮ መስራት አስፈላጊ መሆኑንም ርእሰ መስተዳድሩ አስታውቀዋል።

አቶ ገላሳ ዲልቦ በበኩላቸው ድርጅታቸው የሚያደርገው ትግል እርስ በእርስ ለመጠላለፍ ሳይሆን ለመደጋገፍ ነው ብለዋል።

በቀጣይም እጅ ለእጅ በመያያዝ እና በመደጋገፍ የኦሮሞን ህዝብ ትግል ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ለማሸጋገር እንሰራለን ማለታቸውን የዘገበው ኤፍቢሲ ነው።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *