loading
በአሜሪካ የጆ ባይደን መመረጥ በአፍሪካ ተስፋንም ጥርጣሬንም ይዞ መጥቷል ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ህዳር 02፣ 2013 በአሜሪካ የጆ ባይደን መመረጥ በአፍሪካ ተስፋንም ጥርጣሬንም ይዞ መጥቷል ተባለ፡፡ ጆ ባይደን አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸውን ተከትሎ ዋሽንግተን ከአፍሪካ ጋር ስለሚኖራት ግንኙነት ከወደዲሁ መላ መላ ምቶች ተበራክተዋል፡፡ አንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት የባይደን ወደ ስልጣን መምጣት ለአህጉሪቱ ቀና አመለካት የላቸውም በሚባሉት ዶናልድ ትራምፕ ዘመን የሻከሩ ግንኙነቶች ይስተካከላሉ የሚል ተስፋ ሰንቀዋል፡፡

በተለይ በንግድ፣ በደህንነት ጉዳዮች፣ እንዲሁም በሰብዓዊ መብቶች አያያዝና የዲሞክራሲ ግንባታ ስራዎች ላይ ባይደን አፈሪካን ሊያግዙ ይችላሉ የሚል እምነት እንዳላቸው ይናገራሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አዲሱ ተመራጭ ፕሬዚዳንት በሀገር ቤት በትራምፕ አስተዳደር በተዘበራረቁ የውስጥ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ስለሚጠመዱ ወደ ውጭ ለመመልከት ጊዜ ያስፈልጋቸዋል የሚል ግምት አለ፡፡

በተለይ ከ10 ሚሊዮን በላይ አሜሪካዊያንን ያጠቃውና ከ240 ሺህ በላይ የሚሆኑትን ለሞት የዳረገው የኮሮናቫይረስ ቀውስ መልክ እስኪይዝ ድረስ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲያቸው ምን ሊሆን እንደሚችል ብዙም ላይታወቅ ይችላል የሚሉ አሉ፡፡ ባይደን በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት ቃል በገቡለት በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ግን ከአፍሪካ ጋር ተመሳሳይ አቋም እንደሚኖራቸው ተስፋ አለ፡፡ ሀገሬ ከቀሪው ዓለም ጋር የሚኖራት ግንኙነት ወደነበረበት እንዲመለስና ከመላው ዓለም ጋር በጋራ እድትሰራ አደርጋለሁ ያሉትም ንግግር ብዙዎች በተስፋ የሚጠብቁት ነው ተብሏል፡፡ ዘገባው የአፍሪካ ኒውስ ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *