loading
በአማራ ክልል በተለያዩ ወቅቶች የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል ምክክር መጀመሩ ተነገረ

በአማራ ክልል በተለያዩ ወቅቶች የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል ምክክር መጀመሩ ተነገረ፡፡

 በጉባኤው የተገኙት የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለችግሮች የሚመጥን የሕግ ማስከበር ሥራ እንዲኖር ለማስቻል ምክክሩ ለቀጣይ ስምሪቶች ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሁሉም የክልሉ አከባቢዎች እና አጎራባች ስፍራዎች  የሕግ የበላይነት እንዲከበር እና ሕዝቡ የሚፈልገውን ሰላም ለማረጋገጥ የፌዴራል እና የክልሉ ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮች፣ መከላከያ እና ብሔራዊ ደኅንነት ቢሮ በመገኘታቸው ለቀጣይ ስምሪት ከፍተኛ እገዛ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ሲፈጠሩ የቆዩ የፀጥታ ችግሮችን መገምገምን ዓላማ ያደረገው ምክክሩ ለችግሩ የሚመጥን ጠንካራ የሕግ ማስከበር ሥራ ለመሥራት እንደሚያግዝ ታምኖበታል፡፡

ከሰሞኑ በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ አካባቢ የተከሰተውን ግጭት ለመፍታት የተደራጀ ቡድን ወደ አካባቢው ማምራቱም ተነግሯል፡፡

በዳንጉር አካባቢ የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎም በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጃዊ አካባቢ የፀጥታ ችግር መቀስቀሱ ታውቋል፡፡

ይህ ውይይት የፀጥታውን ችግር ለመቆጣጠር እና ለዜጎች አስተማማኝ የፀጥታ ዋስትና ለማረጋገጥ የሚደረግ ምክክር  መሆኑን የአማራ መገኛኛ ብዙሃን ድርጅት ገልጿል፡፡

 

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *