loading
በነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ እሳት ተቀሰቀሰ

በነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ እሳት ተቀሰቀሰ።

በደቡብ ክልል አርባ ምንጭ ዞን የሚገኘው የነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ ትናንት ማምሻውን መነሻው ያልታወቀ ሰደድ እሳት መቀስቀሱ ታውቋል።

ሰደድ እሳቱ በተለይም የእግዜር ድልድይ የሚሰኙትን ሰንሰለታማ ተራሮች እየተዛመተ ነው ተብሏል።

በአካባቢው የሚገኙ የዓይን እማኞች እንደተናገሩት  በፓርኩ የተቀሰቀሰው ሰደድ እሳት በንፋስ ምክንያት በስፋት በመዛመት ላይ ሲሆን ጉዳቱን ለመቀነስ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ፣ የዞኑ ኗሪ ህዝብና በጎ ፈቃደኞች በቅንጅት እየተረባረቡ መሆኑም ታውቋል።

የተቀሰቀሰው ሰደድ እሳት በቁጥጥር ስር ካልዋለ በተፈጥሮ ሃብትና እንሰሳቱ ላይ የከፋ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል ተሰግቷል።

አባያና ጫሞ ሃይቆች ተዳፋት ላይ በ199 ስኴር ማይልስ ስፋት ላይ በ 1966 ዓም የተመሰረተው የታላቁ ስምጥ ሸለቆ ሃይቆች አካል የሆነው ነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ በዓለም አቀፍ ደረጃ በግዙፍ የተፈጥሮ ሃብት የዱር እንሰሳትና አዕዋፋትና መጠነ ሰፊ ስነ ምህዳር ክምችት ያካተተ ነው።

“አፍሪካ ፓርኮች ጥምረት” በተሰኘ ዓለም አቀፍ የተፈጥሮ ሃብትና ስነ ምህዳር ክብካቤ ተቋም የተመሰረተውና ከ10 አስር ዓመታት በፊት ለ ኢትዮጵያ መንግስት የተላለፈው የነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ በርካታ ብርቅዬ እንሰሳትና አዕዋፋት መገኛም ነው።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *