loading
በትግራይ የሰብዓዊ ድጋፍ 86 በመቶ የሚሆን የቆዳ ስፋት በአጋር አካላቶች እንደሚሸፈን ተገለፀ።

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28 ፣ 2013 በትግራይ የሰብዓዊ ድጋፍ 86 በመቶ የሚሆን የቆዳ ስፋት በአጋር አካላቶች እንደሚሸፈን ተገለፀ።
የትግራይ ክልል የህግ ማስከበር ሂደቱ በኋላ የሰብዓዊ ድጋፍ 3.7 ቢሊዮን ብር ወጪ በማድረግ ለማዳረስ እየተሞከረ መሆኑናይህም የሰብዓዊ ድጋፎ ግን አልተዳረሰም የሚለውን ብዥታ እደሚያጠራው የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገልጿል።
በኢትዮጲያ በኩል ቀሪው 14 በመቶ የቆዳ ስፋት ይሸፈናል ነው የተባለው።ከኢትዮጵያ ጋር የበይነ መንግስታት ስምምነት ያላቸው 4 አጋር አካላት በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ መሆናቸውንና እነዚህም የዓለም ምግብ ፕሮግራም ኬር ወርልድ ቪዥን ኤፍ ኤች መሆናቸው ተነግሯል::

በህግ ማስከበር ሂደቱ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን የስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።ሰላምና መረጋጋት የተረጋገጠባቸው አካባቢዎች ላይ ተፈናቃዮችን እንዲመለሱ ማድረግ ሙሉ በሙሉ ሰላም ያልተረጋገጠባቸው አካባቢዎች ላይ ደግሞ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ካሉ ዘመዶቻቸው ጋር ተጠልለው እንዲቆዩ ማድረግና ከሁለቱም አማራጭ ውጪ ለሆኑ ሰዎች ደግሞ ጊዜያዊ መጠለያ መቋቋም መጀመሩም ተገልፅዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *