በትላንቱ የአውሮፕላን አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ተጓዦች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአካባቢ ጥበቃ ጉባኤተኞች ናይሮቢ ላይ በህሌና ፀሎት አሰቧቸው
በትላንቱ የአውሮፕላን አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ተጓዦች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአካባቢ ጥበቃ ጉባኤተኞች ናይሮቢ ላይ በህሌና ፀሎት አሰቧቸው
በኢትዮጵያ አየር መንገድ በቦይንግ 737-8 ማክስ በበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ወደ ናይሮቢ ሲጓዙ ከነበሩት መካከል ዛሬ ለተጀመረው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአካባቢ ጥበቃ ጉባኤ ላይ ለመካፈል ሲያቀኑ የነበሩ የአደጋ ተጎጅዎች ይገኙበታል፡፡
እናም ለዚህ ጉባኤ መድረስ ያልቻሉት በአደጋው ህይወታቸውን ላጡት ጉባኤተኞቹ የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት በማድረግ ጉባኤያቸውን እንደጀመሩ ሮይተርስ ዘግቧል።