loading
በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ የግዥ ፍላጎታቸውን ያላሳወቁ የመንግስት ባለ በጀት መስሪያ ቤቶች እቃ አቅራቢ ድርጅት አይመደብላቸውም ተባለ

በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ የግዥ ፍላጎታቸውን ያላሳወቁ የመንግስት ባለ በጀት መስሪያ ቤቶች እቃ አቅራቢ ድርጅት አይመደብላቸውም ተባለ

አርትስ 26/03/2011

 ፍላጎታቸውን ያላሳወቁ ተቋማት በማዕቀፍ ስምምነት ግዥ ዕቃ አቅራቢዎች የማይመደብላቸው መሆኑን ያስታወቀው የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ነው።

ኢዜአ እንደዘገበው የመንግስት ባለ በጀት ተቋማት ለሶስት ዓመታት የሚጠቀሙባቸውን የተለያዩ ዕቃዎች ዝርዝር እስከ የካቲት 30 ቀን 2010 ዓ.ም ለአገልግሎቱ ማሳወቅ ነበረባቸው።

ይሁንና ከ142 የፌዴራል መስሪያ ቤቶች ፍላጎታቸውን በወቅቱ ያሳወቁት 82 ብቻ ናቸው። ከ45 ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ 22 ብቻ ናቸው ይህንን ተግባራዊ ያደረጉት።

በአንጻሩ  ፍላጎታቸውን በጊዜ ያላሳወቁ ተቋማት ተወካዮች ‘ውሳኔው ተገቢ አይደለም’ ሲሉ ቅሬታ አሰምተዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *