loading
በሴኔጋል ድንበር አካባቢ በደረሰ የጀልባ አደጋ በርካታ ስተኞች ህይዎታቸው አላፏል ተባለ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2013 በሴኔጋል ድንበር አካባቢ በደረሰ የጀልባ አደጋ በርካታ ስተኞች ህይዎታቸው አላፏል ተባለ:: የተባሩት መንግስታት ድርጅት በመግለጫው እንዳለው በአደጋው ሳቢ 140 ስደተኞችና ናቸው ህይዎታቸው ያለፈው፡፡ ጀልባዋ 200 ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ በድንገት የእሳት አደጋ መከሰቱ ስደተኞቹ ለሞት አደጋ የተዳረጉት ተብሏል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው የሴኔጋል እና የስፔን አሳ አጥማጆችና የባህር ሃይል አባላት ባደረጉት አሰሳ ቀሪዎችን 60 ሰዎች በህይዎት ማትረፍ ችለዋል፡፡በምእራብ አፍሪካ በኩል ወደ ካናሪ ደሴት የሚደረገው አገኛ የባህር ላይ ጉዞ ለበርካታ ህገ ወጥ ስደተኞች ህይዎት መጥፋት ምክንያት እየሆነ ይገኛል፡፡ በዚህ የገገዞ መስመር የሚያቋርጡ ጀልባዎች ሁልጊዜ ከአቅማቸው በላይ የሆኑ ተሳፋሪዎችን ይዘው ስለሚጓዙ ለአደጋ የተጋለጡ ናቸው ተብሏል፡፡

በዚህ ዓመት ብቻ ይህን አደገኛ የጉዞ መስመር በመጠቀም ከ11 ሺህ ያላነሱ ጉዞዎች ወደ ካናሪ ደሴት መደረጋቸውን አይ ኦ ኤም ይፋ አድርጓል፡፡ የሴኔጋል መንግስት ከዓለከም አቀፉ የስደተኞች ተቋመው ጋር በመሆን በህይዎት ለተረፉት ስደተኞች ድጋፍ ለማድረግ ሁኔታዎችን አመቻችቷል ነው ተባለው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *