loading
በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በሃይማኖት ተቋማት መካከል ስመምነት ተፈረመ

የሀይማኖት ተቋማት ለዜጎች በተናጥል የሚያደርጉትን ድጋፍ ውጤት በሚያመጣ መልኩ ለማቀናጀት የሚያስችል ነው የተባለ የመግባቢያ ስምምነት በሃይማኖት ተቋማትና በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተፈረመ።

ሚኒስቴር መስሪያቤቱና  የሃይማኖት ተቋማት አረጋውያንን፣ አካል ጉዳተኞችን እና ለማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት ለማረጋገጥ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ጋር መፈራረማቸውን የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ስምምነቱ ለማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚያስፈልጋቸውን የድጋፍ መስክ በመለየት ድጋፍ ለማድረግና    የሀይማኖት ተቋማት ለዜጎች በተናጥል የሚያደርጉትን ድጋፍ ውጤት በሚያመጣ መልኩ ለማቀናጀት የሚያስችል ነው ተብሏል።

የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ጌታሁን አብዲሳ እንዳሉት የእምነት ተቋማት ለተለያዩ ችግሮች ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያለ ልዩነት አለኝታና መጠለያ በመሆን ቀዳሚ ስፍራ እንደሚይዙ ጠቁመው ይህ የመረዳዳትና የፈጥኖ ደራሽነት ጠንካራ መሠረት መዘመንና ይበልጥ ችግር ፈቺ መሆን ይገባዋል ፡፡

በመሆኑም የእምነት ተቋማት ያላቸውን የዳበረ ልምድ እንደ እርሾ በመጠቀም ስራዎችን ቆጥሮ በሰነድ በማስፈር በቅንጅት ወደ ተግባር መግባት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

የሃይማኖት ተቋማቱ ለማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን መደገፍ አንዱ ተግባራቸው እንደሆነ አንስተው የመግባቢያ ሰነዱ ከመንግስት እንደተገኘ ትልቅ እገዛ በመውሰድ ለውጤታማነቱ እንሰራለን ነው ያሉት፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *