loading
በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን ኮቪድ 19ን ለመከላከል እና ህክምናዉን ለማገዝ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር በጥሬ እና 2 ነጠብ 7 መሊዮን ዶላር በቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸዉ ተገለጸ፡፡

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13 ፣ 2013  በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን ኮቪድ 19ን ለመከላከል እና ህክምናዉን ለማገዝ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር በጥሬ እና 2 ነጠብ 7 መሊዮን ዶላር በቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸዉ ተገለጸ፡፡ ይህ የተገለጸዉ በዶክተር እናዉጋዉ መሀሪ የተመሰረተዉ ፒፕል ቱ ፕፕል የተባለዉ ግብረሰናይ ድርጅት ባዘጋጀዉ ዌቢናር ላይ ነዉ ፡፡በዌቢናሩ ከኮቪድ 19 ጋር በተያያዘ ያለፈዉን አንድ አመት የገመገመና እና የወደፊቱተን አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ዉይይት ተካሄዷል፡፡

በዌቢናሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ኢትጵያ ኮቪድ 19ን ለመከላከል የተለያዩ ስራዎችን የሰራች ሲሆን፤ በዚህም ጥሩ ዉጤት ማግኘት ተችሏል ብለዋል፡፡ በዌቢናሩ የተሳተፉት በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ ፤ኮቪድ 19ን ለመከላከል ከሰሜን አሜሪካ የዲያስፖራዉ ማህበረስብ ከፍተኛ ድጋፍ ተደርገዋል ያሉ ሲሆን አምባሳደሩ ፤ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር በላይ በጥሬ ገንዘብ እና 2 ነጠብ 7 መሊዮን ዶላር በቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ከኮቪድ 19 ክትባት ጋር በተያያዘ ዉይይት የተደረገ ሲሆን ፤የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አስተዋጽኦም ተዳሷል፡፡ በዉይይቱ ከተሳተፉት መካከል ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ና ሳይንስ ሚኒሰትር ዲኤታ ፤ ኡስታዝ አቡበከር ፤ አዜብ ወርቁ ፤ መጋቢ ሀዲስ እሸቱ እና አባገዳ ሰንበቶ ይገኙበታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *