loading
በሩሲያ በደርሰ የአውሮፕላን አደጋ የ41 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

በሩሲያ በደርሰ የአውሮፕላን አደጋ የ41 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

የሩሲያው  ኤሮፍሎት አየር መንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን መንገደኞችን አሳፍሮ በረራ ከጀመረ በኋላ ባጋጠመው የቴክኒክ ብልሽት ለማረፍ መገገዱ ተገልጿል፡፡

አውሮፕላኑ ለማረፍ እየተንደረደረ ባለበት ወቅት ከአውሮፕላኑ የሞተር ክፍል እሳት መነሳቱን ነው አየር መንገዱ ያስታወቀው፡፡

በአደጋውም በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ 41 መንገደኞች ህይወታቸው ማለፉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

አደጋው ህይወታቸውን ካጡት መካከል  ሁለት ህጻናትና አንድ የበረራ አስተናጋጅ መኖራቸውንም ዘገባው አመላክቷል፡፡

አውሮፕላኑ 73 መንገደኞችና አምስት የአውሮፕላኑን ሰራተኞች አሳፍሮ ነበር ሲጓዝ የነበረው፡፡

37 ሰዎች ከአደጋው መትረፋቸው የተነገረ ሲሆን 33ቱ መንገደኞች ሲሆኑ አራቱ የአውሮፕላኑ ሰራተኞች መሆናቸው ታውቋል፡፡

አምስት ሰዎች ወደ ሆስፒታል ተወስደው ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑንም ዘገባው አስታውቋል፡፡

የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑንም የአደጋ አጣሪ ቡድኑ ይፋ አድርጓል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *