loading
በማዕከላዊ አፍሪካ ምርጫ በተከሰተ ብጥብጥ 800 የምርጫ ጣቢያዎች መዘጋታቸውን የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን አስታወቀ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 20፣ 2013 በማዕከላዊ አፍሪካ ምርጫ በተከሰተ ብጥብጥ 800 የምርጫ ጣቢያዎች መዘጋታቸውን የሀገሪቱ የምጫ ኮሚሽን አስታወቀ::
የታጠቁ ሃይሎች ምርጫው በኪካሄድበት ወቅት ባደረሱት ጥቃት 14 በመቶ የሚሆኑት የምርጫ ጣቢያዎችን ለመዝጋት መገደዱን ነው ኮሚሽኑ የገለፀው፡፡
ታጣቂዎቹ በመራጮችና በምርጫ ሰራተኞች ላይ ጥቃት በመሰንዘር፣ እንዲሁም የምርጫ ኮሚሽኑ ስራውን እንዳያከናውን በማገድ ነው ሂደቱን ያደናቀፉት ተብሏል፡፡

የታጠቁ ሃይሎች በመራጮች ከማዋከብ ጀምሮ በአካል ላይ ጉዳት ማድረስ፣ ከፍ ሲልም እስከሞት የሚደርስ ጥቃት መሰንዘራቸውን አልጀዚራ የሀገሪቱን ባለስልጣናት ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ የምርጫ ቀስቀሳው ስራውም አከሁን ቀደም በተቃዋሚዎቹ ማስፈራሪያ ተስተጓጉሎ አንደነበር ተነግሯል፡፡

ከ12 ሺህ በይ የሰላም አስከባሪ ሃይሎች የተሰማሩባት ማእከላዊ አፍሪካ በምርጫው ዋዜማ የሚሊሻዎችን ጠቃት መመከት ችላ የነበረ ቢሆንም ምርጫውን በሰላም ማካሄድ እንዳትችል ያደረሱትን ጥት ቀድማ መከላከል ግን አልቻለችም ነው የተባለው፡፡ ባለፈው ዓርብ ሶስት የሰላም አስከባሪዎች በታጣቂዎቹ ተገደሉ ሲሆን ጥቃት አድራሾቹ ከውጭ ሀገራት የመሳሪያ ድጋፍ ይደረግላቸዋል ሲል የሀገሪቱ የደህንነት ሚኒስቴር ወቀሳ አቀርቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *