loading
በማእከላዊ ናይጀሪያ በአንድ መንደር በተሰነዘረ ጥቃት 14 ሰንፁሃን ዎች ተገደሉ ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ23፣ 2012በማእከላዊ ናይጀሪያ በአንድ መንደር በተሰነዘረ ጥቃት 14 ሰንፁሃን ዎች ተገደሉ ::ጥቃቱ የተፈፀመባት የኮኪ ግዛት ፖሊስ ኮሚሽነር ኢድ አዩባ በሰጡት መግለጫ ከሟቾቹ መካከል አስራ ሶስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው ብለዋል፡፡ድርጊቱን የጅምላ ግድያ በማለት ያወገዙት ኮሚሽነሩ ጣቂዎቹ በድንገት ያደረሱትን ጥቃት ለማጣራት ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

እነዚህ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች የፈፀሙት ድርጊት መነሻ ምክንያቱ ምን እንደሆነ አላወኩም ያለው የግዛቲቱ ፖሊስ የምርመራ ቡድንተቋቁሞ እየሰራ ነው ብሏል፡፡ በሌላ በኩል በአካባቢው ለረጂም ጊዜ ሲነሳ የኖረ የመሬት ባለቤትነት መብት ጥያቄ ስላለ ምናልባት ነገሩ ከዚሁ ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል መላ ምቶች አሉ ነው የተባለው፡፡ በናይጀሪያ በተለያዩ አካባቢዎች ባልታወቁ ታጣቂዎች የሚገደሉ ሰዎች ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ መንግስትን ትልቅ ራስ ምታት እደሆነበር ይነገራል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *