loading
በመኪና አስመራ መሄድ ይፈልጋሉ?

በመኪና አስመራ መሄድ ይፈልጋሉ?

እንግዲያዉስ መነሻቸዉን አዲስ አበባ ያደረጉ አራት መንገዶችን ተጠቀሙ ተብላችኋል፡፡

መንገዶቹንም የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ይፋ ማድረጉን የባለስልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ ተናግረዋል፡፡

የመጀመሪያው መንገድ መነሻውን አዲስ አበባ አድርጎ በአዲግራት እና በዛላምበሳ ዘልቆ አስመራ የሚደርስ ሲሆን 933 ኪሎሜትር ፡፡

በአስፓልት ኮንክሪት ደረጃ የተገነባ ነው፤ ይህ መስመር ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት መስጠትም ይችላል ተብሏል፡፡

ሁለተኛው አማራጭ መስመር ከአዲስ ከአበባ ተነስቶ በመቀሌ፣ በአድዋ፣ በራማ፣ በመረብ አድርጎ ወደ አስመራ የሚያቀናው 1005 ኪሎሜትር የሚሸፍን ሲሆን፥ ከአዲስ አበባ አድዋ ያለው መንገድ በአስፓልት ደረጃ ተሰርቷል፤ ቀሪው ከአድዋ እስከ መረብ ያለው በ2012 እንደሚጠናቀቅም ከባለስልጣኑ ሰምተናል፡፡

ሦስተኛው ከአዲስ አበባ ተነስቶ ጎንደር ሁመራ የሚዘልቀው 991 ኪሎሜትር ርዝመት የሚሸፍን ሲሆን፥ ሙሉ ለሙሉ በአስፓልት የተሸፈነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አራተኛው መዳረሻ ደግሞ መነሻውን አዲስ አበባ በማድረግ በአዋሽ አርባ እና በዴቼቶ አቅንቶ በቡሬ በኩል አሰብ የሚደርስ ነው፤ ይህ መስመር 876 ኪሎሜትር ርዝመት ይሸፍናል፡፡

በአራተኛው መስመር ከአዲስ አበባ ተነስቶ እስከ ዴቼቱ ያለው 659 ኪሎሜትር ሙሉ አገልግሎት መስጠት ይችላል፤ አሁንም ቢሆን አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል ያሉ ሲሆን፥ ከዚያ በኃላ ያለው መስመር ትንሽ የማስተካከል ስራዎችን የሚጠይቅ መሆኑም ተሰምቷል፡፡

የአራቱን አቅጣጫዎች የመንገድ ደህንነት ለመፈተሸ አስፈላጊውን መረጃ ለመሰብሰብ የባለስልጣኑ ሰራተኞች ምልከታ ማድረጋቸውን አንስተው ከአራቱ መካከል የሦስቱ ይዞታ ተሸከርካሪን ማስተናገድ የሚችሉ ነው ብለዋል፡፡

በቀጣይ አዋጭነታቸው እየታየ ሌሎች አማራጭ መንገዶች ሊከፈቱ እንደሚችሉ አቶ ሳምሶን ተናግረዋል፡፡ አሁን ምን ቀረን? አዉቶብሱና ዋጋው ብቻ እሱንም በቅርቡ እንጠብቃለን::

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *