loading
በመተከል ያለዉን የፀጥታ ችግር ከመሰረቱ ለመፍታት የተቀናጀ ኃይል እንዲሰማራ መደረጉን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለጹ፡፡

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 15፣ 2013 በመተከል ያለዉን የፀጥታ ችግር ከመሰረቱ ለመፍታት የተቀናጀ ኃይል እንዲሰማራ መደረጉን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቤንሻንጉል ክልል በመተከል ዞን ያለዉ የጸጥታ ችግር በተለያየ መንገድ ለመፍታት የተቀናጀ ኃይል እንደሰማራ ተደርጓል ብለዋል፡፡ በቤንሻንጉል ክልል መተከል ዞን በዜጎች ላይ እየተፈፀመ ያለዉ ጭፍጨፋ እጅግ ኣሳዛኝ መሆኑን ጠቅላየሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

በወገኖቻችን ላይ በተፈጸመዉ ኢሰባዊ ድርጊትም እጅግ አዝኜለሁ ብለዋል፡፡ ችግሩን በተለያየ መንገድ ለመፍታት ያደረግነዉ ጥረት ሚፈለገዉን ዉቴት አላመጣም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጠላቶቻችን አላማ በህዋሀት,ቡድን ላይ የሰነዘርነዉን ብርቱ ሀይል ለመበተን ነዉ ይህ የሚሳካ አይሆንም ብለዋል፡፡
መንግስት ችግሩን ከመሰረቱ ለመፍታት አስፈላጊ የተቀናጀ ሀይል እንዲሰማራ እንዳደረገ ገልጸዋል፡፡ የሚፈለገዉን ዉቴት ለማግኘት ሁሉም እንደከዚህ ቀደሙ በትኩረትና በህብረት እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *