loading
ሳውዲ አረቢያ ካናዳን ጣልቃ ገብነትሽን አቁሚ ብላታለች፡፡

ሪያድ የካናዳን አምሳደር ከሀገሯ እንዲወጡ ትዕዛዝ አስተላልፋለች፤ የንግድ ግንኙነቷንም አቋርጣች፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበው የሀገሪቱ መንግስት በሳውዲ የካናዳን አምባሳደር ለማባረር ውሳኔ ላይ የደረሰው ሉዓላዊነቴን የሚጋፋ ጣልቃ ገብነት ተፈጸሞብኛል በሚል ምክንያት ነው፡፡
ካናዳ ሳውዲ አረቢያ ያሰረቻቻውን የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እንድትፈታ ያቀረበችው ጥያቄ ነው በሁለቱ ሀገሮች መካካል የተፈጠረውን አለመግባባት ያመጣው ተብሏል፡፡
የሳውዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መስሪያ ቤት በሰጠው መግለጫ የካናዳ ድርጊት ከስድብ አይተናነስም ስለዚህም ፈጣን ምላሽ ያስፈልገዋል ብሏል፡፡
የሳወዲ አረቢያ ግዛት እስካሁን ከየትኛውም ሀገር የሚቃጣበትን ጣልቃ ገብነት ተቀብሎ አያውቅም የካናዳ መንግስትም ይህንኑ ሊገነዘብ ይገባዋል ስትልም ሳውዲ አሳስባለች፡፡
የካናዳ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ሜሪ ፒየር ባሪል (Marie-Pier Baril) በበኩላቸው ሀገራቸው ሁሌም የሰዎችን ሰብዓዊ መብቶች ለማስበር እንደምትቆም አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ ካናዳን ያስቆጣት በተለይ ሳውዲ አሜሪካዊቷን የሰብዓዊ መብት አቀንቃኝ ሳማር በደዊንና ወንድማቸውን ራይፍ በደዊን ማሰሯ መሆኑ በሰፊው እየተወራ ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *