ሰባት ኪሎ ወርቅና በርካታ ዶላር በኮንትሮባንድ ሊገባ ሲል ተያዘ
ክብደቱ ሰባት ኪሎ ግራም የሚመዝን ወርቅና ከፍተኛ መጠን ያለው የዉጭ ሃገር ገንዘብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።
ይኸው ወርቅና ገንዘብ የተያዘው በቶጎ ዉጫሌ ኬላ ላይ በሚሰሩ የጉምሩክ ሰራተኞች ሲሆን በወንጀሉ የተጠረጠሩ አራት ኮንትሮባንድ ነጋዴዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ሚኒስቴሩ የተያዘውን ገንዘብ መጠን ቆጠራው ካለቀ በኋላ አሳውቃለሁ ብሏል።