ሮበረት ኪጉላኒ ለተሻለች ዩጋንዳ እንታገል ሲል ለደጋፊዎቹ ጥሪ አቀረበ ፡፡
አርትስ 9/1/2011
በቅጽል ስሙ ቦቢ ዋይን እየተባለ የሚጠራው ፖለቲከኛ ለህክምና ወደ አሜሪካ ከተጓዘበት ነገ ወደ ሀገሩ እንደሚመለስ አስታውቋል፡፡
አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ዘ ፒፕል ፓወር የተባለው ንቅናቄ መሪ የሆነው ቦቢ ዋይን የሙሴቬኒ መንግስት ከወጣቶች ጋር እንዴት ተስማምቶ መስራት እንዳለበት ስለማያውቅ በጣም ይፈራናል ብሏል፡፡
ታዛቢዎች እንደሚሉት ዩዌሪ ሙሲቪኒ ለመጀመሪያ ጊዜ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስብሰባን አልሳተፍም ማለታቸው ከፖለቲከኛው ወደ ሀገር ቤት መመለስ ጋር ተያይዞ ስጋት ገብቷቸው ነው ይላሉ፡፡
ሙሴቬኒ ግን እዛ ሄጀ የ15 ደቂቃ ንግግር አድርጌ ከምመለስ በሀገሬ በርካታ ስራዎችን ማከናወንን እመርጣለሁ የሚል መልስ ነው የሰጡት፡፡