loading
ሞናኮ ሄንሪን አሰናብቶ ዣርዲምን በድጋሜ ቀጥሯል

ሞናኮ ሄንሪን አሰናብቶ ዣርዲምን በድጋሜ ቀጥሯል

የፈረንሳዩ ሞናኮ በዚህ የውድድር ዓመት በሁሉም ውድድሮች ስኬታማ ጊዜን እያሳለፈ አይገኝም፤ ክለቡ ከወራት በፊት በአሰልጣኝ ሊዮናርዶ ምትክ የቀድሞ ተጫዋቹን ቴሪ ሄንሪን በዋና አሰልጣኝት ቢቀጥርም ውጤት ወደ ክለቡ ሊመጣ አልቻለም፡፡
ይባስ ብሎ ያልታሰቡ አስደንጋጭ ሽንፈቶችን ሲያስተናድ የክለቡ ባለቤቶች ሄንሪን ከስራው አገዱት፤ ወዲያውኑ ደግሞ ክለቡ የቀድሞ አሰልጣኙን ሊሾም መሆኑ ተሰማ፤ አሁን ደግሞ ይህ መረጃ እውነታ መሆኑን የሚያረጋግጥ ዜና ከፈረንሳዩ ክለብ ተሰማ፤ ክለቡን ከወራት በፊት የተሰናበቱትን ፖርቱጋላዊ ሊዮናርዶ ዣርዲም መልሶ ቀጥሯል፡፡
ሞናኮ በሚካፈልባቸው አብዛኛው ውድድሮች የተሰናበተ ሲሆን በሊግ አንድ 19ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
የክለቡ ምክትል ፕሬዚዳንት ቫዲም ቫሲሊዬቭ ጥቅምት ላይ በችኮላ ክለቡን እንዲለቅ የተደረገው ሊዮናርዶ ስራውን እንዲቀጥል ዕድል ተሰጥቶታል ብለዋል፡፡
ቫሲሊዬቭ ‹‹በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት የቡድኑ ቁልፍ ተጫዋቾች መሸጣቸው ዋጋ እንዳስከፈላቸው ተናግረው የእነርሱን ተተኪ ለማምጣት እንደሚሰራ›› ተናግረዋል፡፡
‹‹ቴሪ ሄንሪም ስብስቡ በጉዳት የታጀበ ቢሆንም እንኳ፤ በተጫዋችኑቱ ያሳየንን ድንቅነት በአሰልጣኝነት ሊደግመው ባለመቻ ቡድኑን ከውድቀት ሊታደገው አልቻም›› ብለዋል፡፡
‹‹ተጫዋቾችም የቀድሞ አቋማቸውን በመመለስ ከዣርዲም ጋር ቡድኑን ወደ ላይ ከፍ እንደሚያደርጉት ያላቸውን እምነት›› ተናግረዋል፡፡
የመጀመሪያ የዋና አሰልጣኝነት ጊዜውን በውድቀት የጀመረው ሄንሪ፤ ሞናኮን ከውድቀት ለማንሳትና ዕቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ ጊዜ ሊሰጠው እንደሚገባ ተናግሮ ከአሰልጣኝነቱ መሰናበቱም እንዳስከፋው ተናግሯል፡፡

2017 የፈረንሳይ ሊግ አሸናፊዎቹ፤ ከሄነሪ ጋር በነበሩበት ወቅት በሁሉም ውድድሮች ድል ማድረግ የቻሉት በአምስት ጨዋታዎች ላይ ብቻ ነው፡፡
አዲሱ አሰልጣኝ ዣርዲም በስታዴ ሊዊስ ሁለተኛ አራት አመታትን ከዚህ ቀደም ያሳለፉ ሲሆን፤ አሁን ደግሞ ቡድኑን ለሁለት ዓመት ከግማሽ ለማሰልጠን ተስማምተዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *