loading
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን “መፃዒ የኢንቨስትመንት ኢኒሼቲቭ” ፎረም ላይ ለመሳተፍ ሳውዲ ገቡ

አርትስ 13/02/2011

በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን የሚመራ አንድ ከፍተኛ የመንግስት ልዑክ ከጥቅምት ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ቀናት በሚካሄደው “መፃዒ የኢንቨስትመንት ኢኒሼቲቭ” ፎረም ላይ ለመሳተፍ ሪያድ -ሳውድ ዓረቢያሌሊቱን ገብተዋል።

በዚህ ታላቅ የኢንቨስትመን ፎረም ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ አፍሪካን በመወከል፥ የአህጉሪቱን እምቅ የኢንቨስትመንት አማራጮች እና መፃዒ ዕድሎች በተመለከተ ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለማስተዋወቅ እና አለም አቀፍ ባለሃብቶችን ለመሳብ የሚያግዙ መልዕክቶችን በንግግራቸው ላይ እንደሚያነሱ ጭምር ይጠበቃል።

ከፎረሙ ጎን ለጎን ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ ከሳውዲ ዓረቢያ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነትን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እንደሚኖራቸው  አርትስ ቲቪ ከጉዞው መርሃ-ግብርለመረዳት ተችሏል።

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን በፎረሙ ለመሳተፍ ለሊት ሪያድ ሲገቡ የሳውድ አረቢያ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በክብር ተቀብለዋቸዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *