ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ 14 የሜቴክ የቀድሞ ሰራተኞች ተጨማሪ ከስ ተመሰረተባቸው
ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ 14 የሜቴክ የቀድሞ ሰራተኞች ተጨማሪ ከስ ተመሰረተባቸው፡፡
አቃቤ ህግ ግለሰቦቹ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ከ28 ዓመታት በላይ የተገለገለባቸው አባይ ወንዝ እና አብዮት ከተባሉ ሁለት መርከቦች ግዢ ጋር በተያያዘ ተፈፅሟል ባላቸው የሙስና ወንጀሎች ነው የከሰሳቸው።
ኮርፖሬሽኑ ምንም አይነት መርከብ የማስተዳደር ልምድ ሳይኖረው ሃላፊዎቹ ከሥልጣናቸው አልፈው ተያያዥነት በሌለው ዘርፍ ለመሰማራት መወሰናቸውን የክስ መዝገባቸው ያስርዳል።
በዚህም ኮርፖሬሽኑንና ሀገሪቱን የሚጎዳ ተግባር በመፈፀም ከ544 ሚሊየን ብር በላይ ያለአግባብ ወጪ እንዲወጣባቸው አድርገዋል፡፡
ተከሳሾቹ በአጠቃላይ በመንግስትና በህዝብ የተጣለባቸውን ሃላፊነት ወደ ጎን በመተው በወንጀሉ ድርጊትና በውጤቱ ሙሉ ተካፋይ በመሆን ከ 544 ሚሊየን ብር በላይ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ በማሳጣት ነው ተጨማሪ ክስ የተመሰረተባቸው፡፡