loading
ለህዳሴ ግድብ ከዳያስፖራው የተሰበሰበ ገንዘብ::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 22፣ 2013 ለህዳሴ ግድብ በዚህ ዓመት ከ134 ሚሊዮን ብር በላይ ከዳያስፖራው ተሰበሰበ:: የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባባሪ ብሔራዊ ምክርቤት ጽ/ቤት እንዳስታወቀዉ  ላለፉት 10 ዓመታት ዳያስፖራው በቦንድ ግዢ እና በስጦታ ያደረገው ድጋፍ ከ 1 ነጥብ 5 በሊዮን ብር በላይ ነዉ፡፡

የውሃ ሙሌትተከትሎ በተፈጠረው መነሳሳት ከውጭ እና ከአገር ውስጥ ከፍተኛ ድጋፍ እየተደረገ  ነው፡፡ከዚህ በፊት ተሞክሮ በነበረው የዳያስፖራ ሎተሪ የተወሰነ ገንዘብ ማሰባሰብ ቢቻልም የታሰበውን ያህል ውጤት እንዳላስገኘ ተነግሯል፡፡ በቅርቡ ዘመናዊ የገንዘብ አሰባሰብ ዘዴ በመጠቀም በኢንተርኔት ለግድቡ ድጋፍ የሚደረግበት ድረ ገፅ  በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋ ሆኗል፡፡ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጰያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች  www.mygerd.com የሚል ድረ ገጽ ይፋ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ይህ ዜና እስከ ተጠናቀረበት ድረስ 111 ሺህ 90 ዶላር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በተከፈተው ድረ ገፅ ዳያስፖራው በንቃት በመሳተፍ እና ገጹን በማስተዋወቅ የግድቡን ግንባታ ዳር ለማ ድረስ መረባረብ እንደሚያስፈልግ ነው አቶ ኃይሉ የጠየቁት፡፡በዘንድሮው አመት 1.5 ቢሊዮን ብር ለማሰባሰብ ታቅዶ ከአገር ውስጥ እና ከውጭ በተለያዩ መንገዶች  እስከ ሰኔ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ 2.5 ቢሊየን ብር ድጋፍ ተደርጓል፤ ይህም በአንድ ዓመት የተ ሰበሰበው የመጀመሪያው ከፍተኛው ድጋፍ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በአጠቃላይ እስካሁን ከአገር ውስጥ እና ከውጭ በተለያዩ መንገዶች የተሰባሰበው ገንዘብ 15 ቢሊየን  729 ሚሊየን ብር መድረሱንም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *