ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት እና የከተማዋን ጸጥታ ለማደፍረስ የሚንቀሳቀስ ሀይል የከተማ አስተዳደሩ አይታገስም አሉ ኢንጂነር ታከለ ኡማ
አርትስ 04/01/2011
ምክትል ከንቲባ ኢንጀነር ታከለ ኡማ በነገው ዕለት ለኦነግ አመራሮች የሚደረገው አቀባበል ያለምንም የጸጥታ ችግር እነዲከናወን የከተማ አስተዳደሩ የተሟላ ዝግጅት አድርጓል፡፡
ከዚህ ቀደም የከተማዋ ነዋሪ ከአገር ውጭ የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶችን እና ቡድኖችን በሰላማዊ መንገድ ሲቀበል እንደነበረ አስታውሰው የኦነግ አመራር የሆኑ ወንድሞቹንም በፍጹም ጨዋነት እንዲቀበል ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
አቀባበሉንና ሰንደቅ አላማን ምክንያት በማድረግ በህዝቦች መካከል አላስፈላጊ ግጭት እንዲፈጠር እያደረጉ ያሉ አካላት ላይም አስተዳደሩ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አሳስበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ነዋሪም የኦነግ አመራሮችን ለመቀበል ከ ኦሮሚያ ክልል የሚመጡ ወንድሞቹን በእንግዳ ተቀባይነት ስሜትና በፍቅር ተቀብሎ እንዲያሰተናገዳቸው ጥሪያቸውን አስተላልፈው፤ አቀባበሉ የተሳካና ሰላማዊ እንዲሆን መላው የከተማዋ ህዝብ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም ጠይቀዋል፡፡