loading
ህዝቡ በዓብይ ፆሙ ለሀገር ሠላም ተግቶ ሲፀልይ የነበረውን ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀረበ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22 ፣ 2013የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ርስቱ ይርዳው ህዝቡ በፆም ወቅት ያሳየውን መተዛዘን፣ መከባበርና ለሀገር ሠላምና ደህንነት ተግቶ ሲፀልይ የነበረውን በጎ ተግባር ከፆሙፍቺ በኋላም አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

በክልሉ የትንስዔ በዓልን በማስመልከት ለ970 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታና የእስራት ቅነሳ መደረጉን የገለፁት አቶ ርስቱ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ መልዕክትም አስተላልፈዋል። ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱ ብዙ ፈተና ውስጥ ስለምትገኝ ወቅቱ ስለ ሰላማችን
ተቀራርበን የምንነጋገርበትና የጥፋት ድግሶች በፈጣሪ እገዛ ይብቃ የሚባልበት እንዲሆን ሁሉም በዓሉን ሲያከብር የተቸገሩትን በመርዳትና ያለውን በማካፈል እንዲሆን ያስፈልጋል ብለዋል። አቶ እርስቱ አያይዘውም ከቅርብ ወራት ወዲህ በክልሉ የኮሮና ወረርሽኝ እየተስፋፋ በመሆኑ ህብረተሰቡ
በበዓሉ ወቅት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያርግ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *