loading
ህዝበ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) 44ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ነው፡፡

ህዝበ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) 44ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ነው፡፡

በዓሉ በመቀሌ የሰማዕታት ሀውልት  እየተከበረ ይገኛል፡፡

የምስረታ በአሉ የድርጅቱ ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፣  የፓርቲው እና የክልሉ መንግስት አመራሮች፣ የቀድሞ  ታጋዮች እና የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት ነው እየተከበረ የሚገኘው።

የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ በዓሉን ምክንያት በማድረግ በሰጠው መግለጫ፥ በዓሉ የትግልና ድል ጉዞ የሚዘከርበት ብቻ ሳይሆን ለነገ ትምህርት የሚወሰድበት ቀን እንደሆነ እና ህወሓት ከ44 ዓመት በፊት ትግል ሲጀምር በሀገሪቱ የነበረውን ፀረ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በመገርሰስ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በእኩልነት የሚኖሩባት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመፍጠር ያለመ ነበር ተብሏል፡፡

የ17 የትጥቅ ትግል አመታት ፣አካልና ንብረት መስዋእትነት የተከፈለበት  በዚህም ኢትዮጵያን ከመበታተን በማዳን ባለፉት 27 ዓመታት ወደ አዲስ የልማትና የዴሞክራሲ ምዕራፍ መሸጋገር መቻሉንም መግለጫው አንስቷል፡፡

በዚህም መሰረት የህወሓት 44ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ስናከብር ባለፉት አመታት የተመዘገቡትን ድሎች በመያዝ ሀገራችን ባለፉት 27 አመታት የጀመረችው የለውጥ፣ ሰላምና ብልፅግና ጉዞ ወደኋላ እንዳይመለስ አጠናክረን ለመስራት ቃል በመግባት መሆኑን ከትግራይ ኮሚኒኬሽን ጉዳዩች ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *