loading
ህወሓት በአፋር ክልል በኩል በከፈተው አዲስ ጥቃት ምክንያት እርዳታ ተስተጓጉሏል

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2014 ህወሓት በአፋር ክልል በኩል በከፈተው አዲስ ጥቃት ምክንያት እርዳታ ተስተጓጉሏል አሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል በኩል በከፈተው አዲስ ጥቃት ምክንያት የሰብዓዊ እርዳታ ጭነው ወደ መቀሌ ሲጓዙ የነበሩ የጭነት ተሽከርካሪዎች ወደኋላ ለመመለስ መገደዳቸው ተገለፀ። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ፅህፈት ቤት እንዳስታወቀው፥
ህወሓት በአፋር በኩል እየፈፀመ ባለው ትንኮሳ እና ወደ መኖሪያ አካባቢዎች ላይ እየተኮሰ ባለው ከባድ መሳሪያ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ሰዎች ተፈናቅለዋል።

በዚህ ትንኮሳው እና በፈጠረው የደህንነት ስጋት ምክንያት የሰብዓዊ እርዳታ ጭነው ወደ ትግራይ ክልል በመጓዝ ላይ የነበሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ መግባት እንዳልቻሉና ከግማሽ መንገድ በኋላም ወደኋላ ለመመለስ መገደዳቸውን ነው ያመለከተው። ይህ የህወሓት ድርጊት የሽብር ቡድኑ ለአደገኛ የፖለቲካ ቁማር ሲል ሰላማዊ ህዝብን ለረሃብ እየዳረገ መሆኑን የሚያሳይ ሁነኛ ማስረጃ መሆኑን ጠቁሟል ሲል ፋና ዘግቧል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *