loading
ህወሃትና ሸኔ በሽብርተኝነት ተፈረጁ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28 ፣ 2013 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህወትና ሸኔ በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ አጸደቀ፡፡ ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በሚያካሂደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባው ነው በሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ያጸደቀው፡፡ ሁለቱ ቡድኖች በአገር እና በህዝብ ላይ የሽብር ተግባራትን በመፈፀም ላይ በመሆናቸው በሽብርተኝነት መፈረጃቸው አግባብ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የህወሃትና  ሸኔ ቡድኖች ድርጊት የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣውን ዐዋጅ አሟልቶ በመገኘቱ ነው ምክር ቤቱ በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ የወሰነው ተብሏል፡፡ በዚህም መሰረት የምክር ቤቱ አባላት በአንድ ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ማፅደቃቸውን ከምክር ቤቱ የተገኘው መጀጃ ያመለክታል፡፡ 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ያለው ምክር ቤቱ ተጨማሪ ወሳኔዎችንም ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከሚጠበቁት ውሳኔዎች መካከል የኢትዮጵያ የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅ ይገኝበታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *