loading
ሃገር አቀፍ የመጠጥ ውኃ፣ ሳኒቴሽንና ንጽህና አጠባበቅ ተቋማት ቆጠራ እየተካሄደ ነው

ሃገር አቀፍ የመጠጥ ውኃ፣ ሳኒቴሽንና ንጽህና አጠባበቅ ተቋማት ቆጠራ እየተካሄደ ነው

ቆጠራው የውሃ ተቋማትን ሁለንተናዊ ይዞታ ለማወቅ የሚያግዝና አገልግሎት የማይሰጡ የውሃ ተቋማትን በፍጥነት በመጠገን ችግሮቻቸውን ለመፍታት የሚያግዝ ነው ተብሏል።

የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ እንዳመለከተው ቆጠራው የሚካሄደው ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን በሚቀጥሉት 15 ቀናት ውስጥ ይጠናቀቃል።

ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ እንደተናገሩት የተቋማት ቆጠራ የተጀመረው በአገልግሎት አሰጣጡ ምን ምን ችግሮች በየትኛው አካባቢ እንዳሉ እና በቀጣይ ምን መደረግ እንዳለበት በመረጃ ተደግፎ ለመስራት ነው።

”ቆጠራው የመጠጥ ውኃ ያላገኙ አካባቢዎች የትኞቹ ናቸው? የሚለውን በቀላሉ ለመለየት ያስችላል” ያሉት ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በበጀት አጠቃቀም ላይ የጎላ ሚና እንደሚኖረው አብራርተዋል።

ከዚህ ባለፈም የተቋማት ብልሽት ሲከሰት በፍጥነት ጠግኖ ወደ ሥራ ለማስገባት ቆጠራው ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል።

እንደኢዜአ ዘገባ ቆጠራው የተሳካ እንዲሆን ህብረተሰቡና የጸጥታ አካላት ትብብር እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል ሚኒስትሩ።

የሚኒስቴሩ መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነ በአገር አቀፍ ደረጃ 600 ሺህ የሚገመት የመጠጥ ውኃና የንጽህና ተቋማት ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ።

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *